መግቢያ ለሥራ ፈላጊዎች እና በጎ ፈቃደኞች የዳራ ታሪክ ምርመራዎች

Image
A checklist on a clipboard

ጊዜ

ምርመራዎች ብዙ ጊዜ የሚወስዱ ከሆነ እድሉ ሊያመልጥዎት ይችል እንደሆነ፣ እና ምርመራዎች ከመጠናቀቃቸው በፊት ሥራውን ወይም ስልጠናውን ለመጀመር እድሉ ያለ እንደሆነ ይወቁ።

እድሉ ካመለጠዎት ነገር ግን ለ DBS ምርመራ አስቀድመውኑ አመልክተው ከነበረ፣ ሰርተፊኬት ያገኛሉ እናም ይህ ሌላ ሥራ በቀላሉ ለማግኘት ሊረዳዎት ይችላል።

እምነት እና ተገዥነት

ብዙ የዳራ ምርመራዎች እርስዎ ላይኖርዎት የሚችሉትን መረጃዎች፣ ሰነዶች ወይም ተጠሪዎች እንዲያጋሩ ወይም እርስዎ በማይረዱት ወይም ሊፈሩዋቸው በሚችሉ ሂደቶች ውስጥ እንዲያልፉ መጠየቅን ያካትታሉ።

  • እንዲያደርጉ የሚጠየቁትን እና ለምርመራዎች ከመስማማትዎ በፊት ስለሚያስከትላቸው መዘዞች ተጨማሪ መረጃ ቢጠይቁ ጥሩ ነው።
  • በዳራ ምርመራዎች ውስጥ የተጠየቁትን ነገሮች መረዳትዎን ያረጋግጡ። ብዙ ቃላት ከመደበኛ ትርጉሞች ጋር ተመሳሳይ ያልሆኑ ቴክኒካዊ ትርጉሞች አሏቸው፣ እናም እርስዎ ሊያውቁ የሚችሉበት ምንም ምክንያት አይኖርም።
  • የሚፈልጉትን እድል ካዩ፣ ነገር ግን የዳራ ምርመራ ለመታዘዝ የማይቻል የሚመስል ከሆነ፣ በተቻለ ፍጥነት የምልመላ ሥራ አስኪያጁን ወይም የ ሰው ኃይል አስተዳደሩን፣ ማነጋገር ወይም የልዩ ባለሙያ ምክር መፈለግ ተገቢ ነው።

ብዙ ድርጅቶች በጥገኝነት ሥርዓቱ ውስጥ የነበሩ ሰዎች በዳራ ምርመራዎች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ላይረዱ ይችላሉ፣ እናም እነዚህን መሰናክሎች ማሸነፍ ስለሚችሉባቸው የተለያዩ መንገዶች ላያውቁ ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ ለመቀጠል አማራጭ መንገዶች ይኖራሉ።

ኦፊሴላዊ ትርጉም

ማናቸውም የሚጣሩ ሰነዶች መተርጎም ካስፈለጋቸው፣ እንዲረዱዎ ለመጠየቅ ለእርስዎ ደህንነቱ የተጠበቀ ከሆነ መረጃው የመጣበት አገር ኤምባሲ ሊረዳዎት ይችላል።

ቴክኖሎጂ እና ተደራሽነት

ቀጣሪዎች ምቹ ቦታ እና በማንኛውም ምርመራዎች ውስጥ ለመሳተፍ የሚያስፈልጉትን መሳሪያዎች ሊሰጡዎት እና ለመሳተፍ ማንኛውንም ወጪ መሸፈን አለባቸው። የሥራ ማዕከላት፣ ቤተመጻሕፍት ወይም የማህበረሰብ ማዕከላት ኮምፒዩተሮችን እንዲያገኙ እና ጥሩ የኢንተርኔት ግንኙነትን ሊሰጡዎት ይችሉ ይሆናል፣ ይህም ምርመራዎችን በተቻለ መጠን በቀላሉ ለማከናወን ይረዱዎታል።

ትራዉማ እና ደህንነት

የዳራ ምርመራዎች በግል ሚስጢር ጣልቃ የሚገቡ የሆኑ፣ አስቸጋሪ ትዝታዎችን እና ስሜቶችን የሚቀሰቅሱ ሆነው ሊያገኙዋቸው፣ ወይም የሚጠየቁትን ለማክበር ከባድ ሊሆን እንደሚችል ሊገነዘቡ ይችላሉ።

በሂደቱ ውስጥ በጥሩ ሁኔታ ለመቆየት ምን ሊረዳዎት እንደሚችል ያስቡ። ለምሳሌ፣ አንድን ሰው ይዘው መምጣት ከቻሉ ወይም ሂደቱ በአንድ የተወሰነ ቦታ ላይ እንዲካሄድ ማድረግ ሊረዳ ይችላል።

ስለ ታሪክዎ ወይም በሂደቱ ስላጋጠመዎት ፈተና የግል የሆነ ነገር ማካፈል ከፈለጉ፣ ምን እንደሥራገሩ እና እንዴት አስቀድመው እንደሥራገሩ ማቀድ ሊረዳዎ ይችላል።

ምርመራዎች የተወሰነ ጊዜ ከወሰዱ ወይም ቤት ማዛወር ከፈለጉ፣ መደበኛ ምልመላ ያላቸው ወይም የዝውውር እድሎችን የሚያቀርቡ ሥራዎችን መምረጥ ውጥረትን ሊቀንስ ይችላል፣ እንዲሁም የሚያጠፉትን ጊዜ እና እድል ይቀንሳል።

የዳራ ምርመራዎችን በሚያመቻቹ ሰዎች ላይ መጥፎ ልምድ ካጋጠመዎት እና አስተያየት ለመስጠት ደህንነት የሚሰማዎት ከሆነ፣ ይህ ችግሩን ለመፍታት ይረዳል እንዲሁም በሰዎች እና በሂደቱ ላይ እንደገና እምነት እንዲያገኙ እድል ይሰጥዎታል። በተመሳሳይ፣ ጥሩ ተሞክሮ ካለዎት ደግሞ ሰዎች ያደረጉትን ጥሩ ነገር እንዲያውቁ ማድረግ ሊረዳቸው ይችላል።

ይህ የመረጃ ሉህ የተጻፈው በ Migration Yorkshire በዲሴምበር 2022 ነው። ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎን ያነጋግሩን እኛም እርስዎን ለመርዳት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፦ admin@migrationyorkshire.org.uk ወይም 0113 378 8188።

በዩኬ ውስጥ ለበጎ ፈቃደኝነት ወይም ለሥራ እድል የሚያመለክቱ ከሆነ፣ ለዳራ ምርመራ ፈቃድ እንዲሰጡ ይጠየቃሉ። እነዚህ ምርመራዎች የሚያስፈሩ ሊሆኑ ይችላሉ፣ በተለይም ያለዎት ጉልበት፣ በራስ መsተማመን ወይም ጊዜ ትንሽ ከሆነ።

መጀመሪያ አከባቢ የዳራ ምርመራዎችን ማለፍ ከባድ ሊሆን ይችላል። ይህ የመረጃ ሉህ ለእርስዎ አስፈላጊ የሆኑ እድሎችን ማረጋገጥ እንዲችሉ የምርመራዎችን ተግዳሮቶች ለመቋቋም እንደሚረዳዎት ተስፋ እናደርጋለን።

የዳራ ምርመራዎች ምንድን ናቸው?

የዳራ ምርመራዎች በሠራተኛ ወይም በበጎ ፈቃደኛ ምልመላ ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች እርስዎን ከሚያውቁ ሰዎች የበለጠ ለማወቅ የሚሞክሩበትን የተለያዩ መንገዶች ይገልፃሉ። ይህም እንደሚከተሉት ያሉ ተግባራትን ሊያካትት ይችላል

  • ማንነትዎን ማረጋገጥ

  • ተዛማጅነት ያላቸውን የምስክር ወረቀቶች ወይም የብቃት ማረጋገጫዎችዎን መፈተሽ

  • የሚያውቁዎትን ሰዎች በባህሪዎ ወይም በሥራዎ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ መጠየቅ (ይህ በዋቢነት ይታወቃል)

  • ማንኛውንም የወንጀል መዝገቦችን መመርመር

  • ስለ ጤናዎ መረጃ ከዶክተርዎ መጠየቅ።

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ የዳራ ምርመራዎች የሚካሄዱበትን መንገድ ለመረዳት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል፣ በተለይም የሚፈለገው ነገር በተመሳሳይ ድርጅት ውስጥ እንኳን ከሥራ ወደ ሥራ ሊለያይ ይችላል።

ለምንድነው ንግዶች እና ድርጅቶች የዳራ ምርመራ የሚያደርጉት?

  • በዳራ ምርመራዎች፣ አንድ ድርጅት አንድን ሥራ ለእርስዎ ለመስጠት በራስ መተማመን እንዲሰማው የሚያግዝ መረጃ ለማግኘት ይመክራል። ባሉ ግብዓቶች፣ ስልጠና እና ድጋፍ የሚሰጥዎትን ሥራ ለራስዎ እና ለሌሎች ደህንነት በሚያስጠብቅ መንገድ መወጣት እንደሚችሉ እርግጠኛ መሆን አለባቸው።

  • አንዳንድ የዳራ ምርመራዎች የሚደረጉት፣ አንድ ድርጅት ሕጻናትን ወይም አቅመ ደካሞችን ሊበድሉ የሚችሉ ወይም ለደህንነት ስጋት የሚፈጥሩ ሰዎችን ለመለየት ህጋዊ ግዴታ ስላለበት ነው።

  • አንዳንድ የዳራ ምርመራዎች ሙያዊ ደረጃዎችን ለማሟላት ይከናወናሉ።

በዳራ ምርመራዎች ውስጥ ምን ምርጫ አለኝ?

  • የዳራ ምርመራዎች በሚደረጉበት ጊዜ፣ ለሁሉም እጩዎች ተመሳሳይ የዳራ መረጃ እንዲጠየቅ ሕግ ያስገድዳል።

  • ለዳራ ምርመራዎች ሁል ጊዜ ፈቃድ እንዲሰጡ ሊጠየቁ ይገባል፣ ነገር ግን ፈቃድዎን ካልሰጡ፣ ምናልባት ሥራውን ላይሰጥዎት ይችላል ማለት ነው።

የንግድ ድርጅቶች እና ድርጅቶች ህጎች ምንድ ናቸው?

  • ድርጅቶች ሊጠይቁዎት የሚችሉት እና የማይችሉት መረጃ እንዲሁም ምን እንደሚያደርጉት በህግ ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ይሆናል። ለመቅጠር የሚደረገው የዳራ ምርመራዎች መረጃ እንደ ሆም ኦፊስ ላሉ ሌሎች ባለስልጣናት አይጋራም
  • ከማመልከትዎ በፊት ድርጅቶች ለአንድ ሥራ ምን አይነት የዳራ ምርመራዎች እንደሚደረጉ ግልጽ ማድረግ አለባቸው። እንዲሁም አመልካቾች ስለ ሂደቱ ሊያናግሯቸው ወይም ማናቸውንም ጥያቄዎች ሊጠይቋቸው የሚችሏቸው ሰዎች ስም ያካተተ መረጃ ዝርዝርን ድርጅቶች ማቅረብ ይኖባቸዋል።
  • የዳራ ምርመራዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚጀምሩት የምልመላ ሂደትን ‘ካለፉ’ በኋላ እና ሥራውን መውሰድ እንደሚፈልጉ ከተናገሩ በኋላ ነው።
  • ድርጅቶች የዳራ ምርመራዎችን ወጪ መሸፈን አለባቸው። ከዋጋ ጋር ችግር ካጋጠመዎት፣ ሊረዳዎ ከሚችለው ቁልፍ ሠራተኛ ወይም ከሥራ ማዕከል አማካሪ ድጋፍ ይጠይቁ።

ማንነትዎን ማረጋገጥ

ለአገር እንግዳ ሲሆኑ ወይም በጥገኝነት ስርዓት ውስጥ ሲሆኑ ማንነትዎን ማረጋገጥ ከባድ ሊሆን ይችላል። ማንነትዎን በቀላሉ እንዲያረጋግጡ ለማድረግ ግን ሊወስዷቸው የሚችሏቸው እርምጃዎች አሉ።

  • ከተፈቀዱ የማሳወቅ እና የማገድ አገልግሎቶች (Disclosure and Barring Services) ዝርዝር ውስጥ አንዳንድ ሰነዶችን ለማግኘት ይሞክሩ።
  • በተቻለ መጠን፣ ሂሳቦች ወይም መደበኛ ደብዳቤዎች በሙሉ ስምዎ እንዲደርሱልዎ ይጠይቁ እና በትክክል መጻፉን ያረጋግጡ። በሰነዶችዎ ውስጥ ያሉ ስህተቶችን በተቻለ ፍጥነት ያስተካክሉ።
  • ቀደም ሲል የስደተኛ ደረጃ ካለዎ እና መግዛት የሚችሉ ከሆነ፣ ወይም አንድ ቁልፍ ሠራተኛ ገንዘብ ሊሰጥዎት ከቻለ፣ ለጊዜያዊ መንጃ ፈቃድ ይመዝገቡ

የምስክር ወረቀቶች ወይም ብቃት ማረጋገጫዎች

ብቃት ማረጋገጫዎች ካሉዎት፣ እንዴት እንዲጣሩ እና እንዲረጋገጡ ማድረግ እንደሚችሉ ይወቁ። በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ተመሳሳይ ብቃት ማረጋገጫዎች እና ልምዶች ምን ተብሎ እንደሚጠሩ እና ሰዎች ስለእነሱ እንዴት እንደሥራገሩ ይወቁ። ይህ የበለጠ እንዲረዱ ይረዳዎታል።

አንድ ድርጅት የእርስዎን ብቃት ማረጋገጫዎች ማረጋገጥ ካልቻለ፣ ብቁ የሆኑበት አገር ኤምባሲ ሊረዳዎ ይችላል። እርስዎ በመጡበት አገር ያሉ ሙያዊ ድርጅቶች የእርስዎን ብቃት ማረጋገጫዎች እና በሙያው ውስጥ ስላሳለፉት የአፈጻጸም መረጃ ማረጋገጥ ይችላሉ።

በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሉ ሙያዊ ድርጅቶችም ቀጣሪዎች በእርስዎ ብቃት ማረጋገጫዎች እንዲተማመኑ መርዳት ይችሉ ይሆናል።

ዋቢዎች

ከእርስዎ ጋር ዝምድና የሌላቸው ወይም ለተወሰነ ዓመታት እርስዎን በሙያ ወይም በግል የሚያውቁ ሰዎችን ስም እና አድራሻ እንዲያቀርቡ ሊጠየቁ ይችላሉ። ድርጅቱ እነዚያን ሰዎች በማነጋገር ስለ ሥራዎ ብቁነት አንድ ነገር እንዲናገሩ ይጠይቃቸዋል።

ለአገሪቱ እንግዳ የሆኑ ሰዎች የዋቢ መስፈርቶችን ለማሟላት መቸገር የተለመደ ነው።

  • ከቁልፍ ሠራተኛ ጋር በቅርበት የሚሠሩ ከሆነ ወይም ልጆች ካሉዎት እና በትምህርት ቤታቸው ያሉ ሠራተኞች እርስዎን የሚያውቁ ከሆነ፣ የባህሪ ዋቢ ሊሰጡ ይችላሉ።
  • ዋቢ ማቅረብ ካልቻሉ፣ የምልመላ ሥራ አስኪያጁን ያነጋግሩ። በተወሰኑ ሥራዎች ውስጥ፣ ሀሳባቸውን ሊቀይሩ እና በተመቻቸ ሥራ ወይም በክትትል ሰር ሆነው እንዲጀምሩ ሊፈቅዱልዎ ይችላሉ። ከባለሙያ ምክር መጠየቅ ያስፈልጋቸው ይሆናል።
  • ዋቢ ሊሆኑልዎ የሚችሉ ሰዎች ከሌሉዎት፣ ወደፊት ዋቢ ሊሆኑዎት በሚችሉ ሰዎች እንድታወቁ ዋቢ የማያስፈልገውን ሥራ መውሰድን ማሰብ ይችላሉ።
  • ወደፊት ዋቢዎች፣ ሊሆኑ የሚችሉ የሚያገኟቸውን ሰዎች ስም እና አድራሻ ዝርዝር ከያዙ እና በበጎ ፈቃደኝነት የሚሠሩበትን ወይም በእንግሊዝ ውስጥ የሚሠሩበትን ቀናት፣ ሥራዎች እና ድርጅቶች መዝግቦ ከያዙ ሊጠቅም ይችላል።

የወንጀል መዝገብ ምርመራዎች

ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ ጎልማሶች እና ህጻናት ጋር ልዩ ግንኙነት እንዲኖርዎት የሚያስገድዱ ሥራዎች ላይ ካመለከቱ፣ ወይም ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ እንዲያስተዳድሩ የሚያስችልዎት ቦታ ላይ ካመለከቱ፣ የሚከተለው ሊከሰት ይችላል፦

  • የወንጀል ሪከርድ እንዳለብዎ ሊጠየቁ ይችላሉ
  • በባህሪዎ ምክንያት ምንም አይነት ሥራ ላይ እንዳይሠሩ ቅጣት ተሰጥትዎት ወይም ሥራውን ከመሥራት ታግደው እንደሆነ ሊጠየቁ ይችላሉ።

  • ለማሳወቅ እና የማገድ አገልግሎቶች (Disclosure and Barring Service) ምርመራ - በሌላ መልኩ 'DBS ምርመራ' በመባል ለሚታወቀው ወይም የወንጀል መዝገቦች ምርመራ እንዲስማሙ ሊጠየቁ ይችላሉ።

የማሳወቅ እና የማገድ አገልግሎት (Disclosure and Barring Service) በዩኬ ውስጥ ስለወንጀል መዛግብት መረጃን ማግኘት የሚችል እና ተዛማጅ የሰዎችን መዝገብ የሚያሳዩ የምስክር ወረቀቶችን ለቀጣሪዎች የሚያቀርብ ኦፊሴላዊ ድርጅት ነው። ለሚያመለክቱበት ሥራ የሚስማማ መረጃ ብቻ እንዲጋራ የተለያዩ የ DBS ምርመራ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን የወንጀል ሪከርድ ቢኖርዎትም መሥራት ወይም በበጎ ፈቃደኝነት መሥራት ይችላሉ፣ ነገር ግን የተወሰኑ ሥራዎችን ለመሥራት አይፈቀድልዎትም። ሲጠየቁ፣ በህጋዊ መንገድ የሚፈለጉትን ማንኛውንም መዝገቦች ማቅረብ አስፈላጊ ነው። ምን መጠየቅ እንደሚችሉ እና ምን ማጋራት እንዳለብዎት በሚመለከት ህጎች አሉ። ከተጠራጠሩ መመሪያን ይጠይቁ።

በህገወጥ የሰዎች ማዘዋወር ወንጀል ወይም ወደ ጥገኝነት በሚያደርጉት ጉዞ ላይ ለህልውና ሲሉ ላደረጉት ነገሮች በወንጀል ተከሰው ከነበረ፣ በምልመላ ጊዜ ስለ ጉዳዩ እንዴት መነጋገር እንደሚቻል ለመወያየት ከጠበቃ፣ ከአማካሪ ወይም ከታመነ የጉዳይ ሠራተኛ ጋር ይሥሩ።

እንደ ሂደቱ አካል፣ የማሳወቅ እና የማገድ አገልግሎቱ (Disclosure and Barring Service) እንደ ኦፊሰላዊ የማንነት ማረጋገጫ ሰነዶች የሚያውቃቸው ሰነዶች ተጠቅመው ማንነትዎን እንዲያረጋግጡ ይጠየቃሉ።

ብዙ ሰዎች በራሳቸው ስህተት ባልሆነው ነገር፣ የወረቀት መስፈርቶችን ለማሟላት ይታገላሉ። አስፈላጊውን ወረቀት ማቅረብ ካልቻሉ፣ አሁንም የጣት አሻራዎን ከፖሊስ ጋር በመመዝገብ DBS ምርመራ ማግኘት ይችላሉ።

  • ከ 16 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው የኢሚግሬሽን ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን፣ ወይም በአገሪቱ ውስጥ የቆዩበት ጊዜ ምን ይሁን ምን፣ የ DBS ምርመራ ማግኘት ይችላሉ።
  • የአንድ ሰው ዳራ ምንም ይሁን ምን፣ ማመልከቻው በትክክል ከተደረገ፣ ምርመራው እስኪሠራ ድረስ አብዛኛውን ጊዜ ሁለት ሳምንታትን ይወስዳል።  ወደፊት ሊፈልጉት ከሚችሉት ሥራ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የምርመራ ደረጃ የሚጠይቅ በጎ ፈቃደኝነት ውስጥ መሳተፍ፣ ልምድ እና ዋቢዎችን ለመገንባት ሊረዳዎ ይችላል፣ እናም በሚያመለክቱበት ጊዜ የ DBS ምርመራ አለዎት ማለት ነው።
  • ለ DBS አመልክተው ከነበረ፣ የ DBS ሰርተፍኬትዎን ወቅታዊ ለማድረግ ለ DBS የዝማኔ አገልግሎት (Update Service) መመዝገብ ይችላሉ። ይህ ማለት የወደፊት አሠሪዎች ወይም የበጎ ፈቃደኞች አስተዳዳሪዎች አዲስ ምርመራ ሳይጠይቁ ሰርተፍኬትዎን ማረጋገጥ ይችላሉ። ለበጎ ፈቃደኞች ለእድሳት ምንም ወጪ አይጠየቅም።
  • ይህ ከ Disclosure and Barring Service የወጣው የውጭ አገር አመልካቾች መመሪያ እርስዎን እና ለመቀላቀል የሚያመለክቱትን ማንኛውንም ድርጅት ሊረዳ ይችላል። ለበለጠ መረጃ የ DBS ምርመራዎችን የሚመለከት መረጃችንን ይመልከቱ።

ዓለም አቀፍ ምርመራዎች

ለአንዳንድ ሥራዎች (እንደ ማስተማር ወይም ነርሲንግ) አንድ ድርጅት በውጭ አገር በኖሩባቸው ቦታዎች የወንጀል ታሪክ እንዳለዎት ማወቅ ሊያስፈልገው ይችላል። ለተለያዩ አገሮች የተለያዩ ዝግጅቶች ይኖራሉ። ለተለያዩ አገራት 'የመልካም ባህሪ ሰርተፍኬት' እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ መረጃ በዩኬ መንግስት ይሰጣል።

ቀጣሪዎች የዳራ ምርመራ ማድረግ ካልቻሉ፣የሥራ ቅጥር አቅርቦት ከመወሰናቸው በፊት በተቻለ መጠን ብዙ መረጃዎችን በዋቢ መልክ ማግኘት ይጠበቅባቸዋል።

ምርመራ እርስዎ በኖሩበት ሌላኛው አገር ውስጥ ላሉ ባለስልጣናት ያሉበትን ቦታ ስለሚያሳውቅ ለአደጋ ሊጋለጡ የሚችሉ ከሆነ፣ በድርጅቱ ውስጥ ካሉ የሰው ሀይል (HR) ጋር መነጋገር ወይም የህግ ምክር መጠየቅ ይችላሉ።

ችግር ፈቺ

በተመሳሳይ ጊዜ ድርጅቶች በአስተማማኝ ሁኔታ ለመሥራት ሲፈልጉ፣ ከተለያዩ ዳራ የመጡ ሰዎችም እንዲያመለክቱ ማድረግ አለባቸው። ችግሮች እና ሊኖሩ የሚችሉ መፍትሄዎች ከተጠቆሙ፣ ብዙውን ጊዜ ችግሮች ሊፈቱ ይችላሉ።

Logo for Asylum Migration and Integration Fund

Logo for Refugee Integration Yorkshire and Humber

Contact us

For more information, please contact us at:
admin@migrationyorkshire.org.uk

Source URL: https://www.migrationyorkshire.org.uk/refugee-integration-yorkshire-and-humber/our-translated-resources/introduction-background-checks-job-seekers-and-volunteers