ለመሳተፍ የሚያስፈልጉት ሙያዎች ምን ምን ናቸው?

Image
A pile of notes about employment

ዳራ 


የተፈናቃዮች ተሳትፎ የተለያዩ ነገሮች ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ፤ እንደ አብነት ያህል 'በተሞክሮ ኤክስፐርቶች' ወይም
'የተጠቃሚ ተሳትፎ'። በአንድ የተወሰነ ልምድ ውስጥ የኖሩ ሰዎች አገልግሎቶቹን የሚደግፉበትን መንገድ እንዴትመልክ
እንደሚያሲዙ ይገልጻል።

ለምን መሳተፍ አስፈለገ? 


በተሳትፎ እንቅስቃሴዎች፣ ክህሎቶችዎን ማዳበር እና አገልግሎቶች እንዴት እንደሚሰሩ በተሻለ መረዳት ይችላሉ።
ድርጅቶች የተሻለ የተፈናቃይ ማህበረሰቦችን እንዲያገለግሉ ለማድረግ ሊጠቀሙበት የሚችሉበት ብዙ እውቀት
አለዎት። የእርስዎ እውቀት እና ልምድ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ይረዳል።
በመሳተፍ በራስ -መተማመን ስሜትን ማሳደግ፣ ከተፈናቃይ አገልግሎቶች ጀርባ የሚደረገውን ማየት እና
ማህበረሰቦችዎን ወክለው መናገር ይችላሉ። እንደ ተግባቦቶች፣ ማዳመጥ፣ የህዝብ ንግግር፣ መጻፍ፣ የአመራር ችሎታ እና
ሌሎችም ያሉ ክህሎቶችን መለማመድ ይችላሉ።
ለተፈናቃዮች ማህበረሰቦች ነገሮችን የተሻለ ለማድረግ ወይም አዲስ ክህሎቶችን ለማግኘት ስለሚጓጉ መቀላቀል ይፈልጉ
ይሆናል። አንዳንድ ድርጅቶች እርስዎ ባለዎት ልዩ ክህሎት ወይም የተፈናቃይ ድምጾችን ማካተት ስለሚፈልጉ
እንዲቀላቀሉ ሊጠይቁዎት ይችላሉ።

ተሳትፎ የሚሰራው እንዴት ነው? 


የተፈናቃይ ተሳታፊ ለመሆን የማመልከቻ ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ ሊጠየቁ ይችላሉ፣ አሊያም የተወሰኑ ክህሎቶች
እንዲኖርዎት ሊጠየቁ ይችላሉ። እነዚህ መስፈርቶች ለብዙ ሙያዊ ሚናዎች መደበኛ ሲሆኑ ሚናውን መወጣት
እንደሚችሉ የሚያሳዩበት መንገድ ናቸው። ለምሳሌ ያህል፣ የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ሊጠይቁዎት ይችላሉ፦

  • ለተወሰነ ጊዜ ለሚና እና ለመገኘት ቁርጠኝ መሆንን
  • ከድርጅቱ ጋር ያለውን ግንኙነት መቀጠል
  • ለመማር ፈቃደኛ መሆን
  • ሰዎች የተለያየ ባህልና እምነት እንዳላቸው መቀበል
  • የእውቂያ ዝርዝሮችዎን ማጋራት
  • የማጣቀሻ አድራሻ ዝርዝሮችን ማቅረብ ማጣቀሻው ጓደኛ፣ የቀድሞ ባልደረባ ወይም ሌላ የሚያውቅዎት ሰው ሊሆን ይችላል
  • በዩኬ ውስጥ ተፈናቃይ ስለመሆን ያሳለፉትን የህይወት ተሞክሮዎን ያካፍሉ፣ ግን ይህ ግዴታ አይደለም። ለማጋራት ያልተመቸዎትን ማንኛውንም ነገር እንዲያጋሩ በጭራሽ አይገደዱም
  • እንግሊዝኛ ለመናገር የተወሰነ ችሎታ ይኑርዎት (በተወሰነ ደረጃ)፣ ነገር ግን ሌሎች ቦታዎች አስተርጓሚዎችን ሊያቀርቡልዎት ይችላሉ
  • የDBS (የፖሊስ ፍተሻ) ሰርተፍኬት ያግኙ

ድርጅቶች በእነዚህ እርምጃዎች ይረዱዎታል። ከማመልከትዎ በፊት ከቡድኑ አባላት ጋር ለየሚነጋሩበት እድል
ይኖርዎታል እና እነሱ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ መስጠትም ይችላሉ።
ለተሳትፎ እድል ካመለከቱ በኋላ ሚናውን ለእርስዎ ለማስረዳት የመግቢያ ስብሰባ ይኖርዎታል እንዲሁም ደግሞ ስለ
ሚናው ስልጠና ሊያገኙ ይችላሉ። በአንዳንድ ቦታዎች ስለ አይቲ መሳሪያዎች እና ስለ አጠቃቀም ስልጠና
ይሰጡዎታል።
ያስታውሱ፣ እንደ የጉዞ ወጪዎች ወይም የውሂብ ወጪዎች ካሉ እንቅስቃሴዎች ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ወጪዎች
ተመላሽ መጠየቅ የሚችሉ ይሆናል፣ ግን የራስዎን ገንዘብ ከማውጣትዎ በፊት ለተመላሽ የተሸፈኑ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልግዎታል። እንዲሁም ማበረታቻዎች ሊሰጡዎት ይችላል፤ እነዚህም ማበረታቻዎች ገንዘብ-ነክ ወይም ገንዘብ-ነክ ያልሆኑ ሊሆኑ ይችላሉ።

ከተሳትፎ በፊት ምን እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው? 


ሚናው የተቀየሰው በዩኬ ውስጥ ተፈናቃይ የመሆን ልምድዎን መሰረት በማድረግ የእርስዎን አስተያየት ለማግኘት
ከሆነ፣ ማንኛውንም የተሳትፎ ፕሮጀክት መቀላቀሉ ቀላል ሂደት መሆን አለበት።
ያስታውሱ፣ እድል ለማግኘት ከመመዝገብዎ በፊት ስላሉት ሚናዎች ያለዎትን ማናቸውንም ጥያቄዎች መጠየቅ
ይችላሉ። ለምሳሌ ያህል፦ እንቅስቃሴዎች የትና መቼ ይከናወናሉ፣ እንዴት በመደበኛነት? መጓዝን ይጠይቁኛል? ለራስዎ
እና ለማህበረሰብዎ ምን ጥቅሞች አሉት? ምን አይነት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስፈልጋል እና የአስተርጓሚ አገልግሎቶች
ይሰጣሉ? የልጆች እንክብካቤ ወጪዎችን ይሸፍናሉ? 
እንዲሁም ከመመዝገብዎ በፊት ሚናውን ለመወጣት ጊዜ እንዳለዎት ግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎት።

የተሳትፎ ጥቅሞች ምንድናቸው? 


1. የተግባቦት ክህሎቶችዎን ያሳድጉ፦

  • መሳተፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎቶችዎን ለማሻሻል ይረዳል፣ ይህም ሚናዎ እንዲያድጉ ብቻ ሳይሆን በእለት ተእለት እንቅስቃሴዎ እና ከተለያዩ ባህሎች ካላቸው ሰዎች ጋር ባለዎት ግንኙነት እንዲግባቡ ይረዳዎታል።

  • ስለ የማዳመጥ ክህሎቶች እና የህዝብ ንግግር ስልጠና ሊያገኙ ይችላሉ።

  • ይሁን እንጂ፣ የእንግሊዘኛ ክፍሎችን የሚፈልጉ ከሆነ በዮርክሻየር እና በሃምበር እንግሊዝኛ መማሪያ ድህረ ገጽ ማግኘት ይችላሉ

 

2. ስለ ዜና፣ መመሪያ እና በዩኬ ውስጥ ስላለው ህይወት ህጎች መረጃ ይሁኑ፦

 

  • ከተፈናቃይ ውህደት እና ከተፈናቃይ ማህበረሰቦች ጋር የተያያዙ ርዕሶችን ከሚያሳውቁ ከድርጅቶች ዜናዎችን እና ዝመናዎችን ለመቀበል የአካባቢያችሁን የተፈናቃይ ድርጅቶች ማግኘት ይችላሉ።

3. የግዳጅ ስደት ካጋጠማቸው እና የተፈናቃይ ማህበረሰቦችን ወክለው መናገር ከሌሎች ይማሩ፦

 

  •  ተፈናቃዮች ስጋቶቻቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲገልጹ ከሚረዷቸው ድርጅቶች የተወጣጡ መሳሪያዎችን እና መመሪያዎችን መመልከት ይችላሉ። እንደ የስደተኞች ደህንነት የጋራ ምክር ቤት፣ (The Joint Council for the Welfare of Immigrants)፣ እና የCRÈME ፕሮጀክት መረጃ ወረቀቶች (Project Info Sheets)፣ እና OnRoad Media ያሉ

4. ታሪክን ወይም የተፈናቃዮችን እውነታ ለማካፈል ከሚዲያ ጋር ይሳተፉ፦

 

  • በነጻ ስልጠና ላይ ተገኝተው በመገናኛ ብዙሃን እና ለተፈናቃዮች ተሟጋችነት IMIX፣ እና Refugee Action ማን እንደሚሰራ ማወቅ ይችላሉ

 

5. የእርስዎን ማህበረሰብ እና የአካባቢ ድርጅቶችን ይደግፉ።

 

  • በመሳተፍዎ ድርጅቶች ከቤትዎ እንዲወጡ መገደድዎ ምን እንደሚመስል እንዲረዱ እያበረታቱት ነው፣ እና ይህ አገልግሎቶቻቸውን ከእርስዎ በኋላ ለሚመጡት ሰዎች የተሻለ ለማድረግ ይረዳል።
  • የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ጨምሮ ድርጅቶች ስራቸውን ለመስራት በማህበረሰብ አባላት ድጋፍ ላይ ይተማመናሉ።

Logo for Asylum Migration and Integration Fund

Logo for Refugee Integration Yorkshire and Humber

Contact us

For more information, please contact us at:
admin@migrationyorkshire.org.uk