የወንጀል ሪከርድ ምርመራ በጎ ፈቃደኝነትን እና ሥራን ለሚፈልጉ ሰዎች

Image
Photo of two hands typing on a laptop keyboard

 

በመረጃ ሉሃችን 'የዳራ ምርመራ ለሥራ ፈላጊዎች እና በጎ ፍቃደኞች ' ውስጥ ድርጅቶች ለእርስዎ ሥራ ወይም የበጎ ፈቃደኝነት ሥራ ከማቅረባቸው በፊት የወንጀል ሪከርድ እንዳለዎት እንዲሁም በዩኬ ውስጥ ምርመራዎችን የማካሄድ ኃላፊነት ስላለባቸው
የማሳወቅ እና የማገድ አገልግሎት (Disclosure and Barring Service, DBS) ለምን መመርመር እንዳለባቸው ገለጸናል።
ይህ መረጃ ሉህ ስለ ምርመራዎች እና እንዴ ማመልከት እንዳለብዎት የበለጠ ጥልቀት ያለው መረጃ ይሰጣል።

የተለያዩ የDBS ቼኮች ምንድን ናቸው፣ ምንስ መረጃ ነው የሚያጋሩት?

'መሰረታዊ DBS ሰርቲፊኬት' (Basic DBS certificate) ከባድ ወንጀሎችን ወይም ረጅም የእስር ቅጣት ያስከተሉ ወንጀሎችን ያሳያል።
'መደበኛ DBS ሰርቲፊኬት' (Standard DBS certificate) ማንኛውንም ከባድ ወንጀሎች ወይም ተዛማጅ ጥፋቶችን ያሳያል። ግለሰቡ በህጋ ከተገለጸው 'የማገገሚያ ጊዜ' ውጪ እንደሆነ ከታየ አንዳንድ ያለፉ ጥፋቶች በዩኬ ህግ አይገለጹም።
'የተሻሻለ DBS ሰርቲፊኬት' (Enhanced DBS certificate) ከመደበኛ ሰርተፍኬት ጋር ተመሳሳይ መረጃ የሚያሳይ ሲሆን ዋና የፖሊስ መኮንን ጠቃሚ ነው ብለው የሚወስዱትንም ሌሎች የተመዘገቡ መረጃዎችን ያሳያል።
'የእገዳ ዝርዝር ያለበት የተሻሻለ DBS ሰርቲፊኬት' (Enhanced with barred lists DBS certificate) ከተሻሻለው ምርመራ ጋር ተመሳሳይ ነገር የሚያሳይ ሲሆን በእገዳ ዝርዝር ውስጥ ያለ ሰውን መዝገብም ያሳያል። የእገዳ ዝርዝር ጉዳት ያደረሱ ወይም በተጋላጭ ቡድኖች ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም ያላቸው ሰዎች DBS የተያዘ ዝርዝር ነው።
የተመረመሩ መዝገቦች ከኢንተርፖል (አለምአቀፍ)፣ ከዋና ፖሊስ መኮንኖች የወንጀል መዛግብት ቢሮ (ACRO)፡ እና ከዩኬ ጋር የውሂብ መጋራት ስምምነት ካላቸው አገራት የተጋራ መረጃን ጨምሮ፣ ማንኛውንም በፖሊስ ብሄራዊ ኮምፒዩተር ስርዓትላይ ስለእርስዎ የተያዙ መዛግብትን ያካትታል።
አንድ ሰው በዩኬ ውስጥ እንደ ወንጀል ለማይቆጠር ነገር የወንጀል ሪከርድ ካለው፡ በሰርቲፊኬቱ ላይ አይገለጽም

ለ DBS ምርመራ እንዴት ማመልከት እችላለሁ? 

ለመሠረታዊ ምርመራ፡ እራስዎ ኦንላይን ለ DBS ማመልከት ወይም ማመልከቻዎን እንዲያስተባብር ለድርጅት ፈቃድ መስጠት ይችላሉ። ለሁሉም የ DBS ምርመራ ዓይነቶች፡ መልማይ ድርጅት የማመልከቻ ቅጽ ይልክልዎታል።
ቅጹ ለመልማዩ ድርጅት፡ ወይም "ምርመራዎችን “ለተጠናቀቀ” ስልጣን ላለው ልዩ ድርጅት ሊቀርብ ይችላል።
2) ስለራስዎ፣ የኖሩበት ቦታ እና ለመግለፅ የሚገደዱትን ማንኛውንም የወንጀል ሪከርድ መረጃ በማቅረብ ቅጹን ሙሉ በሙሉ ይሙሉ። ቅጹ የዩኬ የቀን እና የስም ቅርጸቶችን እንድጠቀሙ የሚጠይቅዎት ሲሆን፡ የማይተማመኑባቸውን አንዳንድ ቴክኒካል ቃላትን ይጠቀማል። በቅጹ ላይ የሚከሰቱ ስህተቶች መዘግየትን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ፣ ቅጹን በመሙላት ላይ የሚያምኑት ሰው እንዲረዳዎት ማድረግ ይጠቅማል።
ቅጹ ላለፉት አምስት ዓመታት አድራሻዎችን እንዲሰጡ ይጠይቅዎታል።
ጥገኝነት ከመጠየቅ ጋር ያልተያያዘ ረጅም የጉዞ ጊዜ ከነበረ፣ ‘ውጭ አገር’ (abroad) እንዲሁም አገሩን እና ቀናትን መጻፍ ይችላሉ። በባህር ማዶ የኖሩ ከሆነ፣ በቀድሞው አድራሻዎ የመጀመሪያ መስመር ላይ 'ባህር ማዶ (ከአገር ውጪ)' (overseas) ብለው ያስገቡ እና ከዚያ በተሰጡት መስኮች ውስጥ አገሩን እና ቀናትን ያስገቡ።
ጥገኝነት በመጠየቁ ጉዞዎ ውስጥ የመኖሪያ ቤት አጥነት ጊዜያት አጋጥምዎት ወይም ከቦታ ቦታ ወይም ከካምፕ ካምፕ ተዘዋውረው ከነበረ፣ ለዚህ ጊዜ አድራሻ ማቅረብ አይጠበቅብዎትም። ‘ቋሚ መኖሪያ የለም’ (no fixed abode) ‘ከአገር ውጪ’ (abroad) ወይም ‘ቋሚ መኖሪያ የለም – ዩኬ’ (no fixed abode – UK) በማለት ይህ ሁኔታ ውስጥ የነበሩበትን ቀናት መጻፍ ይችላሉ። ዘመናዊ ባርነት (ህገወጥ የሰዎች ዝውውር)፣ የኢሚግሬሽን እስራት ወይም ሌሎች በቅጹ ላይ ለመግለፅ የሚከብዱ ሁኔታዎች አጋጥመውዎት ከሆነ፣ ቅጽዎን ከማስገባትዎ በፊት ምክር ለማግኘት የ DBS የእገዛ መስመርን ማነጋገር ሊጠቅም ይችላል።
ማስታወሻ፦ በኢሚግሬሽን እስራት ውስጥ ከነበሩ እና ይህ ከተጠረጠረ ወይም ከተከሰሰ ወንጀል ጋር ያልተገናኘ ከሆነ፣ ይህ የወንጀል ሪከርድ አይደለም እና እሱን መግለጽ አያስፈልግዎትም።
3) ከ DBS የተፈቀደ ዝርዝር ውስጥ ኦሪጅናል ሰነዶችን በማቅረብ የማንነትዎን ማረጋገጫ ማሳየት አለብዎት። ይህን ማድረግ ካልቻሉ፣ በምትኩ የጣት አሻራዎችን ማስገባት ይፈልጋሉ የሚል አማራጭ አለ።
ለምርመራ ዓላማ የጣት አሻራዎችን ለማቅረብ ደስተኛ መሆንዎን ከገለጹ፣ መልማይ ድርጅት የጣት አሻራ እንደሚያስገቡ ለ DBS የሚነግርበት እና ከዚያ ይህንንም በፖስታ የሚያረጋግጥ አስተዳደራዊ ሂደት ይኖራል። DBS ከአካባቢው ፖሊስ ጋር በመተባበር የጣት አሻራ እንዲወስዱ ይጋብዝዎታል (ይህ ግብዣ በደብዳቤ ወይም በስልክ ጥሪ ሊሆን ይችላል)። ይህ ሂደት የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
ይህ ከፖሊስ ጋር የሚደረግ ግንኙነት እርስዎ በጥርጣሬ ውስጥ ስለሆኑ እንዳልሆነ ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህን አሠራር ማንነትዎን እና መዝገቦችን በሚጠብቅ መልኩ ለማጠናቀቅ የሰለጠኑ ፖሊሶች ስለሚያስፈልጉ ነው። በመስራት ወይም በበጎ ፈቃደኝነት አስተዋፅዖ ለማድረግ እንደሚፈልግ ሰው ከፖሊስ ጋር እየተገናኙ ነውና፣ አዎንታዊ
ግንኙነት ሊደረግልዎት ይገባል። የጣት አሻራ ለመነሳት ወደ ፖሊስ ጣቢያ መሄድ በተግባርም ሆነ በስሜት አስቸጋሪ ሆኖ ካገኙ፣ ወይም የቀጠሮውን ቀን ለማሟላት ይህን ማለት እና አማራጭ የሚኖርዎት እንደሆነ መጠየቅ ይችላሉ። እንዲሁም አንድን ሰው ከእርስዎ ጋር መውሰድ ይችላሉ።
4) አንዴ ቅጽዎ ከገባ እና ማንነትዎ ከተረጋገጠ በኋላ፣ የDBS አገልግሎት በጥብቅ ህጋዊ ደንብ መሰረት የፖሊስ መዝገቦችን ለማጣራት የቀረበውን መረጃ ይጠቀማል። ያለውን መረጃ ይመለከታሉ፣ ምን መገለጥ እንዳለበት ላይ ማንኛውንም ህጋዊ ደንቦች ይተግብሩ እንዲሁም ለሚያመለክቱበት ሥራ ጠቃሚ ሆኖ የሚወሰደውን የሚገልጽ ሰርቲፊኬት ያትማሉ። ይህ የምስክር ወረቀት ወደ እርስዎ ተልኳል።
መልማይዎ እንዲያየው ይጠይቃልበዚህ ጊዜ ሰርቲፊኬቱን ማሳየት አይጠበቅብዎትም፣ ነገር ግን ካላሳዩ እርስዎን ለመመልመል አይችሉም። በሰርቲፊኬትዎ ላይ ስላለ ማንኛውም መረጃ የምልመላ ሥራ አስኪያጁ ሊያናግርዎት ከፈለገ፣ ለእርስዎ ምቹ በሆነ ቦታ እንዲደረግ መጠየቁ ጥሩ ነው። ከስብሰባው በፊት ምክር ለመጠየቅ ወይም በተለይም የቋንቋ ወይም የባህል እንቅፋቶች ካሉ ለድጋፍ የታመነ ሰው ለማምጣት ለመጠየቅ ይፈልጉ ይሆናል።
5) ለ DBS ማሻሻያ አገልግሎት ለመመዝገብ ያስቡ። ይህ የእርስዎን የ DBS ሰርተፍኬት ወቅቱን የጠበቀ እንዲሆን ያደርጓል እናም የወደፊት መልማዮች ሰርቲፊኬትዎን እንዲፈትሹ ያስችላቸዋል። ተመሳሳይ ደረጃ ምርመራ ለሚፈልግ አዲስ ሥራ ካመለከቱ፣ መልማዩ አጠቃላይ ሂደቱን እንደገና እንዲያሳልፉ ከመጠየቅ ይልቅ በዘመነው ስርዓቱ ማረጋገጥ ይችላል። የ DBS ማመልከቻ ቁጥርዎን እንዳገኙ እና ሰርቲፊኬቱ ከተሰጠበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ቀናት ድረስ ማመልከት ይችላሉ (ይህ ለመሠረታዊ ምርመራ የለም)።

በ DBS ላይ እገዛ 

የሚከተሉት ከሆኑ፣ የ DBS የጥያቄ መስመርን (customerservices@dbs.gov.uk 03000 200 190) በማነጋገር እርዳታ ማግኘት ይችላሉ
 በማመልከቻዎ ላይ በትክክል ስለ ምን እንደሚጽፉ ስጋቶች ካሉዎት፡
 አንድ ጥያቄ ለእርስዎ ጠቃሚ እንደሆነ ካላወቁ፡
 በተፈቀደው ዝርዝር ውስጥ የሌለ የማንነት ሰነድ ካለዎት
 ለ DBS ምርመራ በሚያመለክቱበት ጊዜ ሌላ ማንኛውም ጥያቄ ካለዎት።
ትራንስጀንደር ከሆኑ እና የቀድሞ ማንነትዎን ለመልማይ መግለጽ ካልፈለጉ የ DBS ትራንስጀንደር ማመልከቻ ቡድንን ማነጋገር ይችላሉ።

ችግሮች እና ስጋቶች

አለም አቀፍ ምርመራዎች ላይ ያሉ ችግሮች

የመልማዩን የውጭ አገር የመልካም ስነምግባር ሰርተፍኬት መስፈርቶችን ማሟላት ካልቻሉ፣ በከመስፈርቱ ነፃ እንዲደረጉ መጠየቅ ይችላሉ። ይህ ማለት መልማዩ በእርስዎ ያላቸውን እምነት ለመገንባት ሌላ መረጃ ይፈልጋል ማለት ነው። የአደጋ ግምገማ ሊያደርጉ፣ ተጨማሪ ዋቢዎችን ሊያገኙ፣ ሥራውን ሊለውጡ፣ እራስን መግለጽ እንዲፈርሙ ሊጠይቁዎት ወይም ቃለ መሃላ ሊጠይቁ ይችላሉ።
ራስን መግለጽ የወንጀል ሪከርድ እንደሌለብዎት የተፈረመበት የጽሑፍ መግለጫ ወይም በህጋዊ መንገድ መገለጽ ያለበትን ያለዎትን የወንጀል ሪከርድ ማጋራትን ያካትታል።
ቃለ መሃላ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ ነገር ግን መግለጫው በኤውሮፓ ህብረት ውስጥ በተመዘገበ የህግ ጠበቃ ወይም 'የመሃላ ኮሚሽነር' የተመሰከረ፣ የታተመ እና የተፈቀደ ነው። ብዙ መልማዮች ስለእነዚህ እድሎች አያውቁም።

ኦንላይን ላይ ማመልከት ችግሮች ካጋጠሙዎት

ለ DBS ምርመራ ኦንላይን የሚያመለክቱ ከሆነ እና በአድራሻ ታሪክዎ ችግር ምክንያት ማመልከቻዎን ማሻሻል ካልቻሉ ወይም የጥሩ ስነምግባር ሰርቲፊኬት ማቅረብ ካልቻሉ፣ እርዳታ ይጠይቁ። ስጋት ካለዎት፣ የ DBS ምርመራ ለሚሠራ ድርጅት ማቅረብ ይችላሉ ወይም ከ DBS፣ ከመልማይዎ፣ ከቁልፍ ሠራተኛ ወይም ከጠበቃ ድጋፍ መጠየቅ ይችላሉ። እነዚህ ችግሮች አንዳንድ ጊዜ የሚከሰቱት ኤሌክትሮኒክ አሠራሮች ከተሠሩበት መንገድ ላይ ባለ የዲዛይን ችግሮች ምክንያት ወይም ስርዓቱ በተለየ መንገድ የቆዩባቸውን ቦታዎች እንዲመዘግቡ ስለሚፈልግ ነው። እነዚህ ችግሮች አብዛኛውን ጊዘ ሊስተካከሉ ይችላሉ።

የወንጀል ሪከርድ ካለዎት

የወንጀል ሪከርድ ካለዎት Unlockጥፋተኛ ለሆኑ ሰዎች ታማኝ መረጃ እና የምክር አገልግሎት የሚሰጥ ገለልተኛ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው። እንዲሁም በወንጀል ሪከርድ መረጃ ላይ ተመስርተው የምልመላ ውሳኔ ለሚያደርጉ ቀጣሪዎች እና የሰው ኃይል ባለሙያዎች ገለልተኛ እና ሐቀኛ ምክር እና ድጋፍ ሊሰጡ ይችላሉ።

ይህ የመረጃ ሉህ የተጻፈው በዲሴምበር 2022 በ Migration Yorkshire ነው። ማንኛውም አይነት ጥያቄ ካለዎት፣ እባክዎን ያነጋግሩን እኛም እርስዎን ለመርዳት የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፡ admin@migrationyorkshire.org.uk ወይም 0113 378 818

Logo for Asylum Migration and Integration Fund

Logo for Refugee Integration Yorkshire and Humber