ግንኙነቶችን መፍጠር፣ የመቋቋም አቅምን መገንባት ፦ የዮርክሻየር እና የሃምበር የተፈናቃዮች ውህደት ስትራቴጂ - ማጠቃለያ

Image
A young male refugee

መግቢያ

ይህ እትም የተፈናቃዮች ውህደት ዮርክሻየር እና ሀምበር የሰፋ ፕሮጀክት አካል ሲሆን የተዘጋጀው በአውሮፓ ህብረት ጥገኝነት፣ ፍልሰት እና ውህደት ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ይህም ደግሞ አላማው በመላው አውሮፓ ህብረት የፍልሰትን አያያዝ የበለጠ ቀልጣፋ ለማድረግ ነው። የዚህ እትም ይዘት የMigration Yorkshire ብቸኛ ሃላፊነት ሲሆን በምንም መልኩ የገንዘብ ሰጪውን፣ የአውሮፓ ኮሚሽንን ወይም የዩናይትድ ኪንግደም ተጠሪ ባለስልጣን (ዩኬአርኤ) አመለካከቶችን አያንፀባርቅም። የአውሮፓ ኮሚሽንም ሆነ UKRA በዚህ ህትመት ላይ ላለው መረጃ ለማንኛውም ጥቅም ተጠያቂ አይደሉም።

ዮርክሻየር እና ሁምበር ጦርነትን እና ስደትን ለሸሹት መሸሸጊያን የማቅረብ ረጅም እና አኩሪ ታሪክ አላቸው። ክልላችን በተፈናቃዮች እና በጥገኝነት ጉዳዮች ላይ ጠንካራ አመራርን ደግሞ ደጋግሞ አሳይቷል። እንዲሁም ደግሞ በተፈናቃዮች ውህደት ውስጥ የበርካታ ምርጥ ተሞክሮ ምሳሌዎች ቤት ነው። ይሁን እንጂ ብዙ የሚሰራ ነገር አለ። አሁንም በውህደት ውስጥ እንቅፋቶች እና ተግዳሮቶች አሉ።

ይህ በ2022 መጀመሪያ ላይ የተጀመረው የአዲሱ ዮርክሻየርና የሃምበር የተፈናቃዮች ውህደት ስትራቴጂ፣ 'ግንኙነቶችን መፍጠር፣ የመቋቋም አቅምን መገንባት' ማጠቃለያ ነው። ስትራቴጂውን የሚያሳውቁና የሚገልጹትን ራዕይና እሴቶችን እንዲሁም ደግሞ ለክልላችን የተለዩ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ውህደት ያካትታል። የተዘጋጀው ከ300 በላይ ባለድርሻ አካላት ጋር በመመካከር ሲሆን ሙሉ ሰነዱ (በእንግሊዘኛ) በMigration Yorkshire ድረ-ገጽ (www.migrationyorkshire.org.uk) ላይ ይገኛል። ስትራቴጂ በአዲስ ክልላዊ የተፈናቃዮች ውህደት መድረክ በአፅንዖት እየተጤነ ነው።

አዲሱ ስትራቴጂ ከተለያዩ ዘርፎችና ጂኦግራፊያዊ አካባቢዎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትን ለመደገፍ መገልገያ ሆኖ ተቀርጿል። በክልላችን ያለውን የተፈናቃዮች ውህደት መገለጫ ከፍ የሚያደርግ ሲሆን እዚህ ለሚኖሩ ተፈናቃዮች ውጤትን ለማሻሻል ይረዳል። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስትራቴጂያዊ ቅድሚ የሚሰጣቸው ነገሮች ምኞቶች ናቸው እናም በዮርክሻየር እና ሁምበር የተፈናቃዮች ውህደት ራዕያችን አካል ናቸው። ግን ብዙ ምንሰራው ስራ አለ፣ እናም ራዕያችንን እንድንፈጽም እንድትረዱን ተስፋ እናደርጋለን።

ይህ ማጠቃለያ ስትራቴጂውን ለተፈናቃዮች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችና ሌሎች ጦርነትን እና ስደትን በመሸሽ ልምድ ለኖሩ ሰዎች ተደራሽ ለማድረግ እና የውህደቱን ሂደት በባለቤትነት እንዲይዙ ለመጋበዝ ያለመ ነው። እንግሊዘኛን በመማር እና በማሻሻል፣ በጎ ፈቃደኝነት፣ በስልጠና፣ በማጥናት፣ በስራ በመስራት እና በምትኖሩበት ማህበረሰቦች ውስጥ አዳዲስ ሰዎችን በመገናኘት ክልላችንን የሚያበለፅጉ እና የሚጠቅሙ ክህሎቶችን፣ሀሳቦችን እና ልምዶችን እያበረከታችሁ ነው። ክልላችን ጦርነትንና ስደትን በመሸሽ አጋጣሚ የነበራቸውን ሰዎች ተቀብሎ እንዲቀጥል እና የተቻለውን ሁሉ የውህደት አገልግሎቶች እንዲጎለብት ከተባበርን አዲሱ ስትራቴጂ የበለጠ ለማሳካት ይረዳናል።

ራዕይ እና እሴቶች

"ዮርክሻየር እና ሁምበር ተፈናቃዮች ደህንነት የሚሰማቸው እና የሚቀበሏቸው፣ ህይወታቸውን መልሰው የሚገነቡበት፣ ምኞታቸውን የሚያሟሉበት እና ለሚኖሩባቸው ማህበረሰቦች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ባህላዊ ህይወት የሚያበረክቱበት ክልል ነው"

ይህ ራዕይ እኛን እንደ ክልል በሚገልጹ የእሴቶች ስብስብና የተፈናቃዮች ውህደትን ለማስቻል፣ አገልግሎቶቻችንን፣ መመሪያችንን እና ለተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ያለን አመለካከት ጨምሮ የምናደርገውን ነገር ሁሉ ያሳውቃል። እሴቶቹ ጦርነትን እና ስደትን የሚሸሹ ሰዎች በዮርክሻየር እና በሃምበር ኑሮዋቸውን ሲያመቻቹ አደጋ ላይ ያለውን ነገር በማስታወስ የውህደት እንቅፋቶችን እንድንፈታ ይረዱናል።

የእኛ እሴቶች

  • እንኳን ደህና መጡ - ተፈናቃዮች በሚሰፍሩባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ መጠጊያ እና ድጋፍ ያገኛሉ
  • ማካተት - አገልግሎቶች እና ማህበረሰቦች እንቅፋቶችን ለማስወገድ በንቃት የተሰማሩ ሲሆን የተፈናቃዮችን ፍላጎት ለማሟላት በሚገባ የበቁ ናቸው
  • ትብብር - ባለድርሻ አካላት ጠንካራ እና ዘላቂ ጎኖችን በመገንዘብ በጠንካራ እና ቀጣይነት ባለው አጋርነት አብረው ይሰራሉ
  • ዕድል - ተፈናቃዮች ህይወታቸውን መልሰው መገንባት፣ ምኞታቸውን ማሟላት እንዲሁም ለሚኖሩባቸው ማህበረሰቦች አስተዋፅኦ ማድረግ ይችላሉ
  • እኩልነት - ተፈናቃዮች የተለያየ ባህሪ፣ ፍላጎት እና ምኞት ያላቸው ግለሰቦች እንደሆኑ የሚታወቁ ሲሆን በፍትሃዊነትም ይስተናገዳሉ።

 

 

ስትራቴጂያዊ ቅድሚያዎች

መኖሪያ ቤት እና አካባቢ
  • ሁሉም ተፈናቃዮች ስለ መኖሪያ ቤት አማራጮች፣ መብቶች እና ኃላፊነቶች መረጃን ጨምሮ ወቅታዊና ጥሩ ጥራት ያለው የመኖሪያ ቤት ድጋፍ እና የጥብቅና አገልግሎቶች ማግኘት ይችላሉ።
  • ሁሉም የጥገኝነት መጠለያዎች የአካባቢ ባለስልጣን መስፈርቶችን ያሟላሉ እና የአካባቢው ባለድርሻ አካላት ግዥ እና ተገዢነትን በብቃት መከታተል ይችላሉ።
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በገለልተኛ ወይም ራቅ ባሉ ቦታዎች ወይም በድንገተኛ መጠለያ ውስጥ የሚገኙ በተለያዩ የአቅርቦት አይነቶች አገልግሎቶችን ሊያገኙ ይችላሉ ወይም አስፈላጊ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ የትራንስፖርት ድጋፍ ያገኛሉ።
  • ቤተሰብ-ተኮር ምደባዎች የተንከባካቢ ድጋፍ ላላቸው አብሮ የማይሄድ ጥገኝነት ጠያቂ ልጅ ይገኛሉ
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በአቀባበል እና ተግባቢ ሰፈሮች ውስጥ ይስተናገዳሉ፣ የአካባቢ መረጃን ያገኛሉ እና እንደ ሱቆች፣ መገበያያዎች፣ መናፈሻዎች እና የህዝብ ማመላለሻ ቦታዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠቀም ይችላሉ

 

ኢኮኖሚያዊ ውህደት
  • የተፈናቃዮች ክህሎቶች፣ ብቃቶች እና የስራ ልምድ ተገምግመዋል እና በቀድሞው አጋጣሚ ነው ተለይተዋል
  • ሁሉም ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ድህነትን በመከላከል ረገድ የበጎ አድራጎት ድጋፍ ወይም የድንገተኛ ጊዜ እርዳታ ማግኘት ይችላሉ
  • ተፈናቃዮች የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉና ከአካባቢው የስራ ገበያዎች ጋር የሚጣጣሙ ብጁ እና ዘላቂ የስራ እና የንግድ ልማት ድጋፍ ፕሮግራሞችን ያገኛሉ
  • ተፈናቃዮች ፍላጎቶቻቸውን የሚያሟሉ እና የስራ እድልን የሚጨምሩ የከፍተኛ ትምህርት፣ ስልጠና፣ የበጎ ፈቃደኝነት እና የስራ ልምድ እድሎችን ያገኛሉ #
  • አሰሪዎች እና ቢዝነሶች የተፈናቃዮችን መብቶች እና ፍላጎቶች ያውቃሉ እና የተፈናቃይ ስራን በንቃት ያስተዋውቃሉ

 

ጤና እና ደህንነት
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ከደረሱ በኋላ በተቻለ ፍጥነት ይመረመራሉ፣ ድንገተኛ ህክምና እና ክትባትን ይወስዳሉ፣ እንዲሁም በአካባቢው ዶክተሮች እና የጥርስ ሀኪሞች እንዲመዘገቡ ድጋፍ ይደረግላቸዋል
  • እንደ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ያሉ ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ ቡድኖችን ጨምሮ ተፈናቃዮችና ጥገኝነት ጠያቂዎች መብቶቻቸውን ያውቃሉ፣ NHS እና ማህበራዊ ክብካቤ በክልሉ ውስጥ እንዴት እንደሚሰሩ እና ተስማሚ አገልግሎቶችን ማግኘት እንደሚችሉ ይገነዘባሉ
  • ተፈናቃዮችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የደህንነት ቡድኖችን እና እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ ፍላጎታቸውን የሚያሟላ ጥሩ ጥራት ያለው የአእምሮ ጤና እና የጤንነት አገልግሎቶችን የማግኘት እድል አላቸው
  • ሁሉም የጤና እና ደህንነት አገልግሎቶች የኤንኤችኤስ መመሪያን በመከተል ጥሩ ጥራት፣ ሙያዊ የአስተርጓሚ እና የትርጉም አገልግሎት ይሰጣሉ
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የጤና ማስተዋወቅ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ አገልግሎቶች ያሏቸው ሲሆን አቅራቢዎች የጤና እኩልነትን በማስወገድ ረገድ በንቃት እየተሳተፉ ነው

 

ማህበረሰብ እና አካል መሆን
  • ዮርክሻየር እና ሁምበር፣ በአካባቢያቸው ሰፈሮች፣ ማህበራዊና ማህበረሰብ ቅንብሮች እና የአካባቢ ሚዲያዎች ለተፈናቃዮችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ሁኔታን ያመቻቻል
  • ተፈናቃዮች ከሁሉም አስተዳደግ ከተውጣጡ ሰዎች ጋር ዘላቂ ግንኙነት ይፈጥራሉ እናም ከሌሎች ጋር ለመግባባት ተጨባጭ እድሎችን በመደበኛነት ያገኛሉ
  • ተፈናቃዮችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ያሏቸውን መብቶችና ግዴታዎች ያውቃሉ፣ እናም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ጥራት ያለው የህግ ምክርና ውክልና ማግኘት ይችላሉ
  • ተፈናቃዮች ደህንነት ይሰማቸዋል፣ ከፖሊስ እና ከሌሎች ባለስልጣናት ጋር መተማመንን ያዳብራሉ፣ እንዲሁም ወንጀልን በተለይም የጥላቻ ወንጀልን ስለማሳወቅ እርግጠኞች ናቸው
  • በክልሉ ያሉ የባህል፣ የመዝናኛ እና የስፖርት ዘርፎች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ተደራሽና አቃፊ ስራዎችን በማቅረብ ተፈናቃዮችን በማዋሃድ ላይ በንቃት ተሰማርተዋል

 

ቤተሰቦች እና ወጣቶች
  • ተፈናቃይ እና ጥገኝነት ጠያቂ ህጻናት ወደ እንግሊዝ ከገቡ በኋላ በተቻለ ፍጥነት ትምህርት ማግኘት የሚችሉት ደህንነታቸው የተጠበቀና ተቀባይ በሆኑ ትምህርት ቤቶች እና ኮሌጆች ውስጥ ነው
  • ተፈናቃዮች ከቤተሰብ ፍለጋ እና ከቤተሰብ ዳግም መገናኘት ጋር መረጃ፣ ምክርና ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ እንደ ህጻናትን መጠበቅ እና የቤት ውስጥ ጥቃትን በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ያሏቸውን መብቶች እና ግዴታዎች የሚያውቁ ሲሆን ለባህል ሚስጥራዊነት ያለው ምክር እና የድጋፍ አገልግሎት ያገኛሉ
  • ተስማሚ እና ተደራሽ የሆነ የህጻን እንክብካቤና ሌሎች የቤተሰብ ድጋፍ አገልግሎቶች ለሁሉም የተፈናቃይ ቤተሰቦችና ለሚፈልጉት አባላቶቻቸው ይገኛሉ
  • ወጣት ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ አብሮ የማይሄድ ጥገኝነት ጠያቂ ልጅ እና የእንክብካቤ ፈቃድ ፈላጊዎች ደህንነት ይሰማቸዋል፣ ድጋፍን ያገኛሉ፣ እናም በአዲሶቹ ማህበረሰባቸው ውስጥ የማገገም፣ የማዳበር እና የበለፀጉ እድሎች አሏቸው

 

ቋንቋ እና ተግባቦት
  • የተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የእንግሊዘኛ ቋንቋ ፍላጎቶች ወደ ክልሉ እንደደረሱ በተቻለ መጠን በፍጥነት ወጥ እና አጠቃላይ መሳሪያዎችን በመጠቀም ይገመገማሉ
  • በክልሉ ውስጥ ያሉ ሁሉም የእንግሊዝኛ ለሌላ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች (ESOL) አቅርቦቶች በውጤታማ በፍኖተ ካርታ ተቀምጠዋል እና ተስተዋውቀዋል፣ እና ተፈናቃዮች በአካባቢው ተስማሚ አቅርቦትን ማግኘት ይችላሉ
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ለግል ፍላጎቶቻቸውና ምኞቶቻቸው፣ መደበኛ ያልሆኑ የመማር እድሎችን ጨምሮ የተለያዩ የእንግሊዝኛ ለሌላ ቋንቋዎች ተናጋሪዎች (ESOL) አቅርቦትን ያገኛሉ
  • አገልግሎቶች እና ድርጅቶች ተስማሚ፣ የተተረጎሙ ግብዓቶችን ተደራሽ በሆኑ ቅርጸቶች ጨምሮ ጥሩ ጥራት ያለው እና ሙያዊ የአስተርጓሚ እና የትርጉም አገልግሎቶችን ይሰጣሉ
  • ተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በዲጂታል መንገድ ተካተዋል፣ እናም በኦንላይን አገልግሎቶችን እና ድጋፎችን ለማግኘት የሚያስፈልጉ ክህሎቶች፣ መሳሪያዎች እና ግንኙነት አሏቸው

 

መረጃ እና ውሂብ
  • በዮርክሻየር እና ሁምበር ያሉ አገልግሎቶች እና ድርጅቶች ስለተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች የመረጃ እና የውሂብ ምንጮችን ማግኘት እና በብቃት መጠቀም ይችላሉ
  • አገልግሎቶች እና ድርጅቶች በተፈናቃዮች ውህደት ላይ ውሂብ እና መረጃን አስፈላጊ በሆነበት፣ ከውሂብ ጥበቃ ህግ ጋር በተጣጣመ መልኩ በውጤታማ እና ጠንካራ መንገዶች ይሰበስባሉ፣ ያከማቻሉ እናም ያካፍላሉ
  • በምርምር ማህበረሰቡ እና በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል የቅድሚያ የመረጃ ክፍተቶችን በመለየት እና የምርምር ውጤቶችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማሰራጨት መደበኛ ተሳትፎ እና ትብብር አለ
  • የተፈናቃዮች ማህበረሰቦች በመረጃ፣ በምርምር እና ስለ ውህደት መረጃ በማዘጋጀት ላይ ይሳተፋሉ
  • አገልግሎቶች እና ጣልቃገብነቶች በተፈናቃዮች ውህደት ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ በየጊዜው በአገልግሎት ሰጪዎችና ገለልተኛ ተመራማሪዎች ይገመገማሉ

 

የአገልግሎት እቅድ እና አቅርቦት
  • በአገልግሎቶች ውስጥ ያለው አመራር፣ በተለይም በህዝብ ዘርፍ ውስጥ፣ ለተፈናቃዮች ውህደት እና አቀባበል እና አካታች አገልግሎቶችን ለማዳበር ቁርጠኛ ነው
  • አገልግሎቶቹ ለተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች በጎ እርምጃዎችን ያበረታታሉ፣ እና አቅርቦትን በማግኘት ላይ የሚያጋጥሟቸውን ጉዳቶች ለማስወገድ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ይመድባሉ
  • የተፈናቃዮች ውህደት የኮሚሽን፣ የቅጥር፣ እና መማር እና ልማትን ጨምሮ በአገልግሎት አቅራቢዎች አጠቃላይ ድርጅቶች ውስጥ ተካቷል
  • አገልግሎት ሰጭዎች ሁሉም የሚመለከታቸው ሰራተኞች በተፈናቃዮች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ፍላጎት ላይ በቂ ስልጠና ማግኘታቸውን እና ስልጠናው በመደበኛነት መሻሻሉን ያረጋግጣሉ
  • በዮርክሻየርና ሁምበር ያሉ አቅራቢዎች ሁለንተናዊ አገልግሎቶችን ያዳብራሉ፣ እና በጠንካራ አጋርነት፣ በጠንካራ የሪፈራል ዘዴዎችና በጋራ ተልዕኮ ውጤታማ በሆነ መንገድ እርስ በርስ ይተባበራሉ

 

በፈቃደኝነት እና በማህበረሰብ ዘርፍ
  • በዮርክሻየር እና ሁምበር ያለው የተፈናቃዮች በጎ ፈቃደኝነትና የማህበረሰብ ክፍል በተፈናቃዮች ውህደት ውስጥ እውቀትን እና ግንዛቤን እንዲያዳብር እና እንዲይዝ የሚያስችል ዘላቂ የገንዘብ ድጋፍ አለው
  • በመንግስት እና በግሉ ዘርፍ ያሉ ወሳኝ ባለድርሻ አካላት የተፈናቃይውን VCS ጠንካራ ጎኖች ተገንዝበው ከዘርፉ ጋር በብቃት ይሳተፋሉ
  • በክልሉ ውስጥ ያሉ ሁሉም የሚመለከታቸው አካባቢዎች ንቁ፣ በአግባቡ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የተፈናቃዮች በጎ ፈቃደኞችና የማህበረሰብ ቡድኖች እና ድርጅቶች አሏቸው
  • ዮርክሻየር እና ሁምበር ተፈናቃይ ማህበረሰቦችን በብቃት የሚወክሉ ጠንካራና ስልጣን ያላቸው የተፈናቃይ ማህበረሰብ ድርጅቶች አሏቸው
  • የክልሉ VCS ለተፈናቃዮች፣ ጥገኝነት ጠያቂዎች እንዲሁም ከሌሎች አስተዳደግ ለመጡ ሰዎች ለመዋሃድ አስተዋፅዖ ማድረግ ለሚፈልጉ ትርጉም ያለው የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ይሰጣል

 

ተሳትፎ
  • ተፈናቃዮች ትርጉም ባለው መልኩ በሁሉም ክልል ውስጥ ባሉ የስራ ሃይሎች፣ ቦርዶች፣ አጋርነትና የአመራር ቦታዎች ይወከላሉ
  • ተፈናቃዮች በነባር የተሳትፎ መድረኮች እና ስትራቴጂዎች አገልግሎቶችን እና ድርጅቶችን በመቅረጽ ረገድ ይሳተፋሉ
  • ተፈናቃዮች በገለልተኛ መድረኮች እና በውህደቱ ሂደት ላይ ተጽእኖ በሚፈጥሩ ድርጅቶች ሃሳቦቻውን መግለጽ ይችላሉ
  • አገልግሎቶች፣ ድርጅቶች እና የአካባቢ ማህበረሰቦች የተለያዩ የተፈናቃዮች ቡድኖች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመዋጋት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ፣ እና ለተሳትፎ በቂ ማበረታቻዎችን ይሰጣሉ
  • ተፈናቃዮች በተለያዩ ሚዲያዎች ትረካውን ለመቅረጽ እድሎች ያሏቸው ሲሆን በግዳጅ ስደት እና በክልሉ ጥገኝነት ላይ የህዝብ አመለካከት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ

Logo for Asylum Migration and Integration Fund

Logo for Refugee Integration Yorkshire and Humber

Contact us

For more information, please contact us at:
admin@migrationyorkshire.org.uk